በመረጃ የበለፀገና በመሠረታዊ ተቋማዊ ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ መግባባት ያለው ማህበረሰብ ለመፍጠር ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠንከር አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የሴቶችና የማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለክልል የሴክትር ቢሮ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ሰጥተዋል፡፡

ስልጠናው በየዘርፉ ያሉ ሃገራዊ እንቅስቃሴዎችን፣ ጅምር ጥረቶችን፣ ስኬታማ ተሞክሮዎችንና የተገኙ ውጤቶችን ተከታታይነት ባለውና በተደራጀ አግባብ በሚከናወኑ የተግባቦት ስራዎች ለመደገፍ እንደሚረዳ የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሮ ሐረጓ ማሞ ገልጸዋል፡፡ በመረጃ የበለፀገና በመሠረታዊ ተቋማዊ ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ መግባባት ያለው ማህበረሰብ ለመፍጠር ብሎም እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን አጉልቶ ማሳየትም ይገባል ብለዋል፡፡

በዚህ ረገድም ግንዛቤ ለማስጨበጥ የየክልሉ የሴቶችና ማህበራዊ የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎችና የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በዕለቱ “የሴክተር የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ሚና” በመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት እንዲሁም “የዲጂታል ሚዲያ አጠቃቀምና የኮሚኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች ሚና በሚዲያ” በሚል በጋዜጠኛ መሠለ ገ/ሕይወት የቀረቡ ሲሆን ለተሳታፊዎች በዘርፉ ዙሪያ አቅማቸውን በይዘት አዘገጃጀት በመልክት አቀራረፅ እና በማህበራዊ ሚዲያ መልክት ስርጭት ላይ ጥልቅ ውይይቶችም ተደርገውበታል፡፡

Please follow and like us: