Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የተቋማዊ ስራዎችን በውጤታማ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ተግባራት አጠናክሮ ማስቀጠል የሚያስችል የጋራ ፎረም ተመሠረተ።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከክልል ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬቶችና በ 10ክልሎች በሚገኙ የመገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ላይዘን (የማህበረሰብ ሬድዮ፣የብዙሀን መገናኛ አውታር አስተባባሪዎች)
የተቋማዊ ስራዎችን በውጤታማ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ተግባራት አጠናክሮ ማስቀጠል የሚያስችል የጋራ ፎረም መሠረተ። በምስረታው ላይ ተሳታፊዎች እንደገለፁት ሴክተሩ ቅንጅታዊ አሰራር ያልተጠናከረበት በመዋቅር ደረጃ ወጥ የሆነ የአሰራር ማዕቀፍና እቅድ አለመኖር ፣በቂ የኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች በሴክተሩ አለመኖር ተግዳሮት መሆኑን ጠቅሰዋል።

ነገር ግን ባለው ውስን የሰው ሀይል ስራዎችን ተከፋፍሎ በመስራት የሴክተሩን ግቦች ለማሳካት ከፍተኛ ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑን አንስተዋል። የፎረሙ ምስረታም እንደ ችግር የተነሱትን በተወሰነ ደረጃ እንደሚቀርፍና ቅንጅታዊ አሰራር ለማጠናከር ፣ ወጥ የሆነ እቅድ አንዲኖር ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ጠቅሰዋል ።

በዕለቱ የ2018 የኮሚኒኬሽን መነሻ ዕቅድ ቀርቦ ውይይት የተካሄደበት ሲሆን ይህም የተጣጣመና የተመጋገበ አሠራርን ለመዘርጋት እንደሚያግዝ ተጠቅሷል።
Please follow and like us:
