“ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት” በሚል መሪ ቃል በየደረጃው ለሚገኙ የተቋሙ የስራ ሃላፊዎች የስልጠናና መማማሪያ መድረክ እየተካሄየ ነው

ስልጠናው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፌዴራል የፀረ ሙስናና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።

በመድረኩ ላይ ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ሚኒስቴሩ በተለይ ቤተሰብና ትውልድ ላይ የሚሰራ ተቋም እንደመሆኑ መጠን ትውልዱን በመልካም ስነ-ምግባር ለማነፅ ከቤተሰብም ጀምሮ ማህበረሰቡ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ህዝባዊ ንቅናቄ ማካሄድ ይገባል ብለዋል።በተቋሙ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን ለማሳካት፣ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣትና የሚሠጡ የማህበረሰብ አገልግሎቶችንም ውጤታማ ለማድረግ በየደረጃው የሚገኘው አስፈፃሚ አካል ስነምግባርን በተላበሰ መልኩ ተልዕኮውን መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከኮሚሽኑ ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው ስልጠናውም ከተቋሙ አንፃር ሙስናንና ብልሹ አሰራርን ለመከላከልና ተጠያቂነትን ለማስፈን ለሚደረገው ጥረት ስኬታማነት ትልቅ ዕገዛ እንደሚያደርግ ገልፀዋል። በዚህ ረገድ ኮሚሽኑ እያደረገ ላለው ድጋፍም ክብርት ሚኒስትሯ አመስግነዋል። የፌዴራል የፀረ ሙስናና ስነ-ምግባር ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አቶ ፍቃድ ሰቦቃ በበኩላቸው ሙስና ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮችን የሚያባብስና በዜጎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል እኩይ ተግባር መሆኑን ጠቅሰው አምርሮ መታገል እንደሚገባ አንስተዋል።

ኮሚሽኑ እያንዳንዱ ዘርፍ ለሙስናና ለብልሹ አሰራር ያለው ተጋላጭነት ምን ይመስላል የሚለውን መነሻ በማድረግ ድርጊቱን ለመከላከል ያለመ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐግብር ቀርፆ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል። ምክትል ኮሚሽነሩ ሙስናንና ብልሹ አሰራርን በመከላከል ረገድ ሊወሰዱ ይገባል ያሏቸውን አንኳር ጉዳዮችም በአፅዕኖት አስገንዝበዋል።

የጎንደር ዩኒቨርስቲ ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ አካዳሚክ ዲን እና የጎንደር ስማርት ሲቲ ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ይልቃል ሙሉዓለም የስልጠናው ዓላማ ሙስናንና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የሚያስችል እውቀትና ክህሎት በማስጨበጥና የአመለካከት ለውጥ በማምጣት በየዘርፉ ድርጊቱን እንዲከላከሉ ማድረግ ነው ብለዋል።

Please follow and like us: