Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የሴቶች ህጻናት ወጣቶችንና ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎችን መረጃ ሰው ሰራሸ አስተውሎትን በመጠቀም ማገዝ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ተቀብለው በፅህፈት ቤታቸው አነጋግረዋል፡፡

በውይይቱ ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) እንደገለጹት የሴቶች፣ ህጻናት፣ ወጣቶችንና ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎችን መረጃ ሰው ሰራሸ አስተውሎትን በመጠቀም ማገዝ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ በዚህም አኒስቲቲዩቱ በሚኒሰቴር መስሪያ ቤቱ ሊሰሩ የታቀዱ አሰራሮችን በዲጂታላይዜሽን ለማገዝ፥ ስራን ሊያቀላጥፉ እና ዜጎችን ተጠቃሚ ሊያደርጉ የሚችሉ የአጭር እና የረዥም ጊዜ ሰው ሰራሸ አስተውሎት የምርምር ትግበራ እቅዶችን፣ ስልቶችን እና ፕሮግራሞችን በመንደፍ እንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ፕሮግራምን በመላው ኢትዯጵያ ለሚገኙ ወጣቶች ተደራሽ ለማድረግ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በቅንጅት ለመስራት በሚቻልበት ሁኔታም ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
Please follow and like us:
