Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ሴቶችንና ወጣቶችን በኢኮኖሚ ለማብቃት የሚሰሩ ስራዎች ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጡ በትብብር ለመስራት የጃፓን አለም አቀፍ ትብብር ዝግጁነቱን ገለጸ፡፡
የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የጃፓን አለም አቀፍ ትብብር ዋና ተወካይ የሆኑት ኬሱኪ ኦሺማ ተቀብለው በፅህፈት ቤታቸው አነጋግረዋል፡፡

በውይይቱ ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) እንደገለጹት፣ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በሰፊው የዳሰሱ ሲሆን በተለይም ሴቶችንና ወጣቶችን በኢኮኖሚ የማብቃት ጉዳይ ቀዳሚ የትኩረት መስክ በማድረግ አሁን ላይ በሰፊው እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ በዚህ ረገድ የጃፓን አለም አቀፍ ትብብር እስካሁን እያደረገ ላለው ድጋፍ አመስግነው በእነዚህ የትብብር መስኮችና ሌሎች ዘርፎች ላይ በጋራ እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በኢትዮጵያ የጃፓን አለም አቀፍ ትብብር ዋና ተወካይ ኬሱኪ ኦሺማ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ የልማት አጋር እንደሆነች ጠቅሰው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሴቶችንና ወጣቶችን በኢኮኖሚ ለማብቃት የሚያከናውናቸው ተግባራት ተጨባጭ ውጤት ማምጣት በሚችልባቸው ዘርፎች ላይ በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
Please follow and like us:
