የሚኒስቴሩ አመራሮች እና ሠራተኞች በ2018 ሀገራዊ ዕቅድ ላይ ውይይት አደረጉ

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች በ2018 በጀት ዓመት ሀገራዊ ዋና ዋና የልማት ዕቅድ ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡
‎‎መድረኩን ያስጀመሩት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንደተናገሩት፥ ባለፈው ዓመት እንደ ሀገር በሁሉም የኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ አመርቂ ስኬቶች ተመዝግቧል፡፡ ‎በዚህም የሴቶች፣ የወጣቶችና ድጋፍ የሚሹ የህብረተሠብ ክፍሎች ተጠቃሚነትና ተሣታፊነት ከዓመት ዓመት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ገልፀዋል።
‎ ‎ሀገራዊ ዕድገቱ ከልማት ጋር የተሳሰረ፣ የምንገኝበትን አለም አቀፍ ሁኔታን ታሳቢ ያደረገ፣ የኢኮኖሚ ዕድገቱም ወደ ሰው ህይወት የተጠጋ እንዲሆን በማድረግ ረገድ በትኩረት እየተሠራ እንደሆነም አክለው ተናግረዋል።

‎‎በሚቀጥለው ዓመትም የሴቶችን፣ የህፃናትን፣ የወጣቶችን የአረጋውያንና የአካል ጉዳተኞችን እንዲሁም ድጋፍ የሚሹ የህብረተሠብ ክፍሎችን ሁለንተናዊ ተሣትፎና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ዕቅዱን ከተቋሙ አኳያ በመቃኘት በጥብቅ ዲሲፒሊን መፈፀም ያስፈልጋል ብለዋል።‎የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ በበኩላቸው፥ የ2018 በጀት አመት ሀገራዊ ዕቅዱን በዝርዝር አቅርበው ውይይት ተካሂዶበታል።

‎‎እንደ አጠቃላይ ሀገር ልታድግ፤ የተቀመጡ ግቦችም ሊሳኩ የሚችሉት በዜጎች የተቀናጀ አስተዋፅዖና ርብርብ መሆኑን ገልፀው ሁሉም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮችና ሠራተኞች በየደረጃው በየዘርፉ ከሚገኙ አስፈፃሚ አካላት ጋር እየተናበቡ በትጋት ሊሰሩ እንደሚገባ በውይይቱ ወቅት አፅዕኖት ሰጥተዋል።
‎

Please follow and like us: