Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የኢፌዴሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን አስመልክተው ያስተላለፉት መልዕክት
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ7ኛ ጊዜ እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “ነገ በአንድ ጀምበር ታሪክ እንስራ” ሲሉ ባስተላለፋት መልዕክት መሠረት የኢትዮጵያ ህዝብ ከዳር እስከ ዳር በነቂሰ በመውጣት አሻራውን እንደሚያሳርፍ ይጠበቃል።
በመሆኑም የሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን አመራሮችና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አካል በሆነውና ነገ ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በሚካሄደው የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እንደተለመደው ሁሉ ሁላችንም በአንድነት በመውጣትና በንቃት በመሳተፍ ለሀገራዊ ጥሪ ተግባራዊ ምላሽ እንሰጥ። ከተቋማችን ሰራተኞች በተጨማሪ መላው የሀገራችን ሴቶች፣ ህጻናት፣ ወጣቶች፣ አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች በዚህ ታላቅ ሀገራዊ ንቅናቄ ላይ በባለቤትነት በመሳተፍ የዜግነት አሻራችሁን እንድታኖሩ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።
#greenlegacy #700millioninoneday #በመትከልማንሰራራት
Please follow and like us:
