Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ሀገር የምትገነባው በዜጎቿ አብሮነት እና እያንዳንዱ ዜጋ በሚያበረክተው አስተዋፅፆ በመሆኑ የተተከሉ ችግኞች እንዲፀድቁ መንከባከብ ከሁሉም ይጠበቃል- ክብርት ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ከሌሎች ከፍተኛ አመራሮች፣ ሠራተኞችና የተለያዩ አደረጃጀቶች ጋር ከማለዳው ጀምሮ በጉለሌ እፅዋት ማዕከል ቅጥር ግቢ የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር አካሂደዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንደገለፁት፤ የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ኢኒሼቲቭ የሆነው የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ድርሻው የላቀ ነው ሲሉ ገልፀዋል። አክለውም ሀገር የምትገነባው በዜጎቿ አብሮነት እና እያንዳንዱ ዜጋ በሚያበረክተው አስተዋፅፆ ነው ያሉት ክብርት ሚኒስትሯ ችግኞችን የምንተክለውም ሆነ እንዲፀድቅ የምንከባከበው ለራሣችን ብለን መሆኑ መገንዘብ ይኖርብናል ሲሉም ተናግረዋል።
ስለዚህ ችግኞችን ከመትከል ባሻገር እንዲፀድቁ መንከባከብም ይገባል ብለዋል። በዛሬው ዕለትም በችግኝ ተከላ መርሐ-ግብሩ ከተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች በተጨማሪ የአረጋውያንና የጡረተኞች ማህበር፣ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር፣ የወጣቶች ምክር ቤት እና የህፃናት ፓርላማ ተወካዮች መሳተፋቸውን ገልፀዋል።
በመርሐ ግብሩ የአገር በቀል ችግኞች የተተከሉ ሲሆን አኮርች፣ ብርብራ፣ ወይራ፣ ቡና፣ አቮካዶና ሌሎችም ይገኙበታል።
#greenlegacy #700millioninoneday #በመትከልማንሰራራት
