ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች የሚሰጠው የማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት ቅንጅታዊ አሰራሮች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባልም- ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ዘርፍ አራተኛ የጋራ ጉባኤ በቢሾፍቱ እየተካሄደ ነው።
‎‎በጉባኤው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወርቀሰሙ ማሞን ጨምሮ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ የክልል ቢሮ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ አደረጃጀቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
‎‎የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በዚሁ ጊዜ፥ ሴክተሩ በ2017 በጀት ዓመት ለመተግበር ያቀደውን ማሳካት ይችል ዘንድ ከፍተኛ ርብርብ ሲደረግ መቆየቱንና ተስፋ ሰጪ ውጤት ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል።
‎ ‎ሆኖም በሴክተሩ የሚከናወኑ ተግባራት ሰፊና ተመጋጋቢ በመሆናቸው በአንድ ተቋም ወይም በአንድ አካል ጥረት ብቻ የታለመላቸውን ዓላማ ማሳካት አዳጋች መሆኑን ጠቁመዋል። እየታየ ያለውን ጥረትና ጅማሮ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ቅንጅታዊ አሰራርን ይበልጥ አጠናክሮ ከማስቀጠል ጎን ለጎን ጎልተው እየወጡ ያሉ ስኬታማ ልምዶችና መልካም ተሞክሮዎችን በማስፋፋት ለላቀ ውጤታማነት በትጋት መስራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡
‎‎በተለይ በሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ችግሮች ሳቢያ ድጋፍ የሚፈልጉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተደራሽ ለማድረግ የሁሉም አካላት ርብርብ አስፈላጊ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
‎ ‎ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች የሚሰጠው የማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋትም ቅንጅታዊ አሰራሮች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም ገባልም ተናግረዋል።
‎ ‎የዘርፉን ልዩ ባህሪ ተቋቁመው ሰለቸኝ ደከመኝ ሳይሉ ሃለፊነታቸውን በብቃት እየተወጡ ያሉ አስፈፃሚ አካላትንና የሴክተሩን እንቅስቃሴ በተለያዩ አግባብ እየደገፉ ለሚገኙ አጋር ድርጅቶች ምስጋና አቅርበዋል።
‎
‎በበጀት ዓመቱ የሴክተሩን እቅድ ከማሳካት አኳያ የተጓዘበትን ርቀት ለመገምገም፣ ልምድ ለመለዋወጥ፣ ተሞክሮን ለማስፋት እና የቀጣይ አቅጣጫን ለማስቀመጥ መድረኩ የበኩሉን እገዛ ያደርጋል ተብሏል።
‎
‎

Please follow and like us: