የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ከኬንያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም አከናወኑ ፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ከኬንያ ኤምባሲ ጋር በጋራ በመሆን በአዲስ አበባ ከተማ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ለሚገኙ አቅመ ደካማ ዜጎች የማዕድ ማጋራት አከናውነዋል፡፡

በማዕድ ማጋራቱ ሂደት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እንደገለፁት ከኬኒያ ኤምባሲ ጋር በቅንጅት የተደረገው የማዕድ ማጋራት ከዲፕሎማሲው ባሻገር የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን አጠናክሮ ለመቀጠል እንደሚያስችል ገልፀው አንድነታችንን በጠንካራ መሰረት ላይም ያስቀምጣል ብለዋል፡፡ ሚኒስትሯ እንዳሉት በአሁን ወቅት ሀገሪቱ ለዜጎችዋ ትኩረት በመስጠት ከምታከናውናቸው ተግባራት መካከል አንዱ በሆነው የማዕድ ማጋራት ላይም ኤምባሲው መቀመጫውን ባደረገበት አካባቢ ያሉ ማህበረሰቦችን ተደራሽ ለማድረግ እንደዚህ አይነቱ መርሃ-ግብር ላይ በመሳተፉ ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል፡፡

በኢትዮጵያ የኬኒያ አምባሳደር ጆርጅ ሞሪንሀ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት እያከናወነች ያለችው ልማት ለጎረቤት ሀገሮችም ምሳሌ እየሆነ መምጣቱን ገልፀው በተለይ የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ዘርፈ-ብዙ ጥቅሞችን ለቀጠናው እንደሚያበረክት ተናግረው የማዕድ ማጋራቱ ላይም በመሳተፋቸው የተሰማቸውን ክብር ገልጸው ይህም የወንድማማችነት መገለጫ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
የማዕድ ማጋራቱም አካል ጉዳተኞችን እና አቅመ ደካማ ዜጎችንም ያካተተ ነበር፡፡

Please follow and like us: