Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የተቋሙን የማስፈየተቋሙን የማስፈፀም አቅም ለማጎልበትና በግብርናው ዘርፍ የሴቶችን የኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ድጋፍ እንደምታደርግ ህንድ አስታወቀች
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማር እና ልዑካን በድናቸውን ተቀብለው አነጋገሩ።
በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማር በዚሁ ወቅት፥ ህንድ በግብርና፣ በአካታች የዲጂታል ፋይናንስ፣ በምግብ ማቀነባበር፣ ምላሽ ሰጪ የስርዓተ ፆታ በጀት አስተዳደር እና በአመራር ዙሪያ ነፃ የትምህርት እድል እንደምትሰጥ አስታውቀዋል። በተጨማሪም በግብርና መስክ የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ሚኒስቴሩ የነደፈው ፕሮግራም ወጤታማ እንዲሆን ህንድ ድጋፍ እንደምታደርግ ገልፀዋል። የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በበኩላቸው፥ የህንድ መንግስት የኢትዮጵያ ጠንካራ የልማት አጋር መሆኑንና ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋርም በተለያዩ መስኮች በትብብር እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የሴክተሩን የማስፈፀም አቅም ከማሳደግ አኳያ ነፃ የትምህርት እድል መመቻቸቱና ሴቶችን በኢኮኖሚ ለማብቃት ህንድ ድጋፍ እንደምታደርግ መግለጿን አድንቀው ክብርት ሚኒስትሯ ምስጋና አቅርበዋል። በቀጣይም ዘላቂነት ያለው አጋርነትን የበለጠ ለማጠናከርና ለጋራ እቅዱ ስኬታማነት በቁርጠኛነት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። ለዚህም በተመረጡ መርሐግብሮች ዙሪያ ድጋፍ ለማድረግ የቀረበውን ሃሳብ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመተግበር የሚያስችል የቴክኒክ ኮሚቴ ለማቋቋምና የመግባቢያ ስምምነት ለመፈራረም መስማማታቸው አያይዘው ገልፀዋል።
የሴክተሩን የማስፈፀም አቅም ከማሳደግ አኳያ ነፃ የትምህርት እድል መመቻቸቱና ሴቶችን በኢኮኖሚ ለማብቃት ህንድ ድጋፍ እንደምታደርግ መግለጿን አድንቀው ክብርት ሚኒስትሯ ምስጋና አቅርበዋል። በቀጣይም ዘላቂነት ያለው አጋርነትን የበለጠ ለማጠናከርና ለጋራ እቅዱ ስኬታማነት በቁርጠኛነት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። ለዚህም በተመረጡ መርሐግብሮች ዙሪያ ድጋፍ ለማድረግ የቀረበውን ሃሳብ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመተግበር የሚያስችል የቴክኒክ ኮሚቴ ለማቋቋምና የመግባቢያ ስምምነት ለመፈራረም መስማማታቸው አያይዘው ገልፀዋል።Please follow and like us: