የጤና ማህበራዊ ልማት ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በመገኘት የስራ ጉብኝት አካሄዱ

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና ማህበራዊ ልማት ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ምቹ የስራ ከባቢ ለመፍጠር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን አስመልክቶ የስራ ጉብኝት አካሂደዋል።
‎የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የተቋሙ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኮሪደር ልማት ምክንያት ቀድሞ ከነበረበት ካዛንችስ በመልቀቅ ወደ አራት ኪሎ ሲገባ ለሰራተኛው እና ለተገልጋዮች ምቹ የስራ ከባቢ ለመፍጠር ሰፊ ስራ ሲሰራ መቆየቱን በመግለፅ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን አስጎብኝተዋል። የጤና ማህበራዊ ልማት ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላትም በጉብኝታቸው የሪፎርም አካል የሆነውንና ምቹ የስራ ከባቢ ለመፍጠር የተደረገውን ጥረትና ቁርጠኝነት አድንቀዋል።
‎‎የሴቶችን፣ የህጻናትንና የወጣቶችን እንዲሁም የአረጋውያንን፣ የአካል ጉዳተኞችን እና ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ብሎም የመረጃ አያያዝን ለማዘመን የሚያግዝ ዳታቤዝ ስርዓት ለመዘርጋት እንዲሁም ስራዎችን ዳጂታላይዝ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን በመጥቀስ ግብረ-መልስ ሰጥተዋል። በቀጣይም በተቋሙ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት አሰጣጥ አሰራር ለመዘርጋት የተጀመሩ ተግባራት ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቀው ወደ ስራ እንዲገቡ ተገቢው ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበትም አሳስበዋል።
‎

Please follow and like us: