የሥራ ከባቢ ምቹነት ሠራተኞችን ለፈጠራ ስራ ከማበረታታት ባሻገር ከእቅድ በላይ የሆኑ ስራዎችን ለመስራት እንደሚያግዝ ጠቆሙ፡፡ የተከበሩ ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ‎

የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ እንዲሁም የቋሚ ኮሚቴው  አባላት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ተዘዋውረው በጎበኙበት ወቅት እንደተናገሩት የሥራ ከባቢ ምቹነት ሰዎችን ለፈጠራ ስራ ከማበረታታት ባሻገር ከእቅድ በላይ የሆኑ ስራዎችን በባለቤትነት ስሜት ለመስራት እንደሚያግዝም ተናግረዋል፡፡

ሰብሳቢዋ አክለውም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሴክተር ተቋማዊ የሆነ ጥንካሬን እያመጣ ያለ ዘርፍ መሆኑን ገልፀው በተለይም በቴክኖሎጂ የተደገፉና ዘመኑን የዋጀ የአሰራር ሂደት በመከተል  ለመተግበር ያለው ተነሳሽነት የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ሚኒስቴሩ በየደረጃው ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደረግ በመሆኑ ከዘርፉ የሥራ ኃላፊዎችና ከክልሎች እንዲሁም  ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራና በቅንጅት በመተባበር‎ የሴቶችን፣ የህፃናትን ፣ የወጣቶችን እንዲሁም የአረጋውያንን፣ የአካል ጉዳተኞችን እና ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የህብረሰተሰብ ክፍሎችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በጋራ የተቀናጀ ስራ መስራት እንደሚገባውም አሳስበዋል።

ቋሚ ኮሚቴው በሴክተሩ የሚከናወኑ ተግባራት ላይ የሚያደርገውን የክትትል፣ ቁጥጥርና ድጋፍ ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል፡፡

Please follow and like us: