Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ለስኬታማ የሪፎርም ትግበራ እና ለጠንካራ ተቋም ግንባታ ተናቦና ቁርጠኛ ሆኖ መስራት ያስፈልጋል
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር የመንግስት አገልግሎት አስተዳደር ሪፎርም ላይ ያተኮረ የክህሎት ስልጠናና የውይይት መድረክ አካሂዷል።
ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በዚህ ወቅት፥ ሀገራችን ኢትዮጵያ ለውጡን ተከትሎ ሁሉን አቀፍ የመንግሥት አገልግሎትና አስተደደር ሪፎርም ተግባራዊ እያደረገችና ውጤትም እያስመዘገበች ትገኛለች። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ግልጽና ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ዘመናዊ እንዲሁም ከብልሹ አሰራር የፀዳና ተጠያቂነት ያረጋገጠ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ስርዓትን ለመገንባት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል። ሚኒስቴሩ እየሠራቸው ያሉ የሪፎርም ሥራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ በማስቻል ረገድ በየደረጃው የሚገኙ የተቋሙ አመራሮችና ፈፃሚው ሠራተኛ ዋነኛ ተዋናይ መሆናቸውን ያነሱት ዶ/ር ኤርጎጌ፤ ስልጠናው ሪፎርሙን በእውቀት እንድንመራ የበኩሉን እገዛ ያደርጋል ብለዋል።

ለስኬታማ የሪፎርም ትግበራም ሆነ ለጠንካራ ተቋም ግንባታ ተናቦና ተባብሮ መስራት አስፈላጊ መሆኑን ስራ አስፈፃሚው አፅዕኖት ሰጥተዋል። በመንግስት አገልግሎት አስተዳደር ማሻሻያ ፖሊሲና ቀጣይ ተግባራት ዙሪያ ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በዶ/ር ወርቁ እና ዶ/ር ታሪኩ አማካኝነት ስልጠና ተሰጥቶ ግንዛቤ እንዲያዝበት የተደረገ ሲሆን ከተሳታፊ ለተነሱ ጥያቄዎች በሚመለከታቸው አካላት ምላሽና ማብራሪያ ቀርቧል።
