‎በአማራ ክልል በ2017 ዓ.ም በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ ከ656 ሺህ በላይ ወጣቶች መሳተፋቸው ተገለፀ።

‎በአማራ ክልል በ2017 ዓ.ም በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ ከ656 ሺህ በላይ ወጣቶች መሳተፋቸውን በምክትል ርዕሰ መሥተዳደር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) ገለፁ።

‎‎የ2017 ዓ.ም የክረምት ወራት ሀገር አቀፍ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማጠቃለያ እና የዕውቅና መርሐ-ግብር “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሀሳብ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው። ‎በማጠቃለያ መርሐግብሩ በምክትል ርዕሰ መሥተዳደር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) እንዳሉት፥ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የመንፈስ እርካታ ለማግኘት ሰዎች በፈቃደኝነት የሚሰጡት እና ተግባሩም የሰዎችን ሰብአዊነት የሚያጎለብት አገልግሎት መሆኑን ተናግረዋል።
‎ እንዲሁም የበጎ ፈቃት አገልግሎት ማኅበራዊ መስተጋብርን እያጠናከረ መሆኑን፣ የልማት ክፍተቶችን በመሙላት እና የማኅበረሰቡን መልካም እሴት በማጠናከር ሚናው እየጎላ መምጣቱን ገልጸዋል።

‎‎በክልሉ በ2017 ዓ.ም በ14 የስምሪት መስኮች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ ከ658 ሺህ በላይ ወጣቶች መሳተፋቸውን ገልጸዋል። ‎በተጨማሪም ከ13 ሚሊዮን በላይ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ እንዲሁም ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆን የመንግሥትን ወጭም መታደግ መቻሉን ገልጸዋል።።

Please follow and like us: