ጥብቅ ማሳሰቢያ!!

‎”ሰናይ ዘመን ትሬዲንግ የጉዞና የቫዛ አማካሪ” ነኝ በሚል ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ፈቃድ እንደተሰጠው በማስመሰል ለዜጎች የካናዳ የስራ ቪዛ ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ እንደሆነና ምዝገባ እንደጀመረ የሚገልፅ ሀሰተኛ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ እንደሚገኝ ለማረጋገጥ ተችሏል።

‎‎ሆኖም ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን በምስሉ ላይ ያለውን አይነት መጠሪያ ስያሜ የሌለውና የሎጎ ብራንድ የማይጠቀም፣ የውጭ ሀገር የስራ ቪዛ አገልግሎትን በተመለከተ ለየትኛውም አካል ፈቃድ የመስጠት ሃላፊነትም ስልጣንም የሌለው መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን። ‎በመሆኑም የሚሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ፣ ሀሰተኛና ህገ ወጥ ተግባር መሆኑን እያሳወቅን ህብረተሰቡ በወንጀለኞችና በአጭበርባሪዎች የተሳሳተ መረጃ እንዳይታለል፣ ራሱን እንዲጠብቅና ምንም ዓይነት ምላሽ መስጠት እንደሌለበት ለማሳሰብ እንወዳለን። ‎ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ሀገር ጋር የተያያዙ ማናቸውም የስራ ጉዞዎችን በተመለከተም ትክክለኛውን መረጃ ከትክክለኛው አገልግሎት ሰጪ ተቋም ብቻ መውሰድ እንደሚገባ በአፅዕኖት ለማስገንዘብ እንፈልጋለን። ‎ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቀጣይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበሮ በህገወጥ ድርጊቱ የተሰማሩ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ እንደሚያደርግ እየገለፀ ህብረተሰቡ ህገወጦችን በንቃት በመከታተል እንዲያጋልጥና እንዲተባበር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዚህ አጋጣሚ ጥሪውን ያቀርባል።

Please follow and like us: