ወጣቱ ሚዛናዊ አስተሳሰብን በማዳበር ለሀገሩ ልማት የድርሻውን ሊወጣ ይገባል – ከንቲባ ከድር ጁሀር

‎የአፍሪካ የወጣቶች ወር የማጠቃለያ መርሐ ግብር “የተለወጠ የወጣቶች የሥራ ባህል፣ ለኢኮኖሚ እመርታ” በሚል መሪ ሀሳብ በድሬዳዋ ተካሂዷል።
‎‎የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ ወጣቱ ከስሜት ይልቅ በሃሳብ የበላይነት በማመን እና ሚዛናዊ አስተሳሰብን በማዳበር ለሀገር ብልፅግና ሚናውን ሊወጣ ይገባል። ‎ወጣቱ ለሀገር እድገት እና ልማት ምሰሶ በመሆኑ በኃላፊነት ስሜት ሀገርን የሚጠቅሙ ተግባራት ላይ መሳተፍ እንዳለበትም አሳስበዋል። ‎የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሙና አህመድ በበኩላቸው፤ የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 ለወጣቶችና ሴቶች ልዩ ትኩረት መስጠቱን አንስተዋል።

‎‎መንግሥትም ይህንን ለማረጋገጥ የብሔራዊ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ረቂቅ ፖሊሲ እና የወጣቶች የዜግነት አገልግሎት ረቂቅ አዋጅ ማዘጋጀቱን ተናግረዋል። ‎በእውቀት፣ በክህሎት እና በሥነ-ምግባር የታነጸ እንዲሁም አገር ወዳድና ሥራ ፈጣሪ ትውልድ ለመፍጠር ቅንጅታዊ አሰራር እንደሚያስፈልግም ተመላክቷል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

Please follow and like us: