Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
20ኛውን የብሔር ብሄረሰቦች ቀን “ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል ተከበረ
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች 20ኛውን የብሔር ብሄረሰቦች ቀን አክብረዋል።በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ክቡር አቶ ጌታቸው በዳኔ በንግግራቸው
በሀገሪቱ በየዓመቱ የሚከበረው የብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን አብሮነትን የሚያጠናክር መሆኑን በማስታወስ። እንደ ኢትዮጵያ ብዝሃን በሚንፀባረቅበት ሀገር ፌዴራሊዝም ብዝኃነትን ባከበረ መልኩ ኅብረብሔራዊ አንድነትን ለመገንባት ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ብለዋል፡፡ ፌዴራሊዝም አንድ የፖለቲካ ሥርዓትን ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ በሕዝቦች ፍላጎትና ምርጫ ለመገንባት የሚያስችል አማራጭ መርህ መሆኑን ተናግረዋል።
በአሉን ስናከብር በአገራችን ዴሞክራሲያዊ ፌደራላዊ ሥርዓት ማእቀፍ የተገነባ ኅብረብሔራዊ አንድነት ሥር እንዲሰድና እንዲዳብር የሚረዱ ግንዛቤዎችን በየደረጃው የሚገኙ ሕዝቦች በዴሞክራሲ እና ፌዴራላዊ ሥርዓት ላይ ግንዛቤ እንዲያገኙ እና ለአገራችን አንድነት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ለማድረግ መሆኑ ነው በማለት ገልጸዋል፡፡ እለቱን በማስመልከት በዴሞክራሲ፣ በፌዴራላዊ ሥርዓት እና በፌዴራላዊ ዴሞክራሲ ምንነት እና ባህሪያት መካከል ያለውን ግንኙነት እና የኢፌዲሪ ሕገመንግስት ዴሞክራሲያዊ ገፅታ እና የፌዴራል ሥርዓት ግንባታ ያሉትን ተስፋዎችና የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቶች ላይ የጹሁፍ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል
