Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የተቋሙ ሰራተኞች ድጋፍ ተበረከተ
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ከቻይና የገጠር ልማት ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ 150 የተቋሙ ሰራተኞች ለእያንዳንዱ አምስት ሊተር የምግብ ዘይትና አስር ኪሎ 1ኛ ደረጃ ዱቄት ድጋፍ አድርጓል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ሰራተኞቹ ለተቋሙ ስኬት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እያበረከቱ መሆኑን በመጥቀስ አመስግነዋል። አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የተቁሙን ሰራተኞች ድጋፉ ወደፊትም ቀጣይነት እንደሚኖረው ተናግረዋል። የቻይና የገጠር ልማት ፋውንዴሽን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችንና ተማሪዎችን ለመደገፍ እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

Please follow and like us:
