‎ሚኒስቴሩ እና ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን በተለያዩ መስኮች ትብብርን ለማጠናከርና በጋራ ለመስራት ተስማሙ

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ የማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ሀገራዊ ፕሮግራም ዳይሬክተር መፍትሔ ታደሰን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

‎‎የስራ ሃላፊዎቹ ሴቶችን በኢኮኖሚ ማብቃት፣ በወጣቶች ስብዕና ግንባታ፣ በአካቶ ትግበራ፣ በአካል ጉዳተኞች ተጠቃሚነት እና ተያያዥ ጉዳዮች ዘሪያ በትብብር ለመስራት የሚያስችል ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል። ‎በቀጣይ ሁለቱ ተቋማት በጋራ በሚያስተሳስሩ የትኩረት መስኮ ዙሪያ አጋርነትን ለማጠናከርና በጋራ ለመስራት የስራ ሃላፊዎች ተስማምተዋል።

Please follow and like us: