የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር 900,ሺህ ብር የሚገመት ድጋፍ ለጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት አበርክተ

ድጋፉ የተደረገው የዘንድሮውን ዓለም አቀፍ የጸረ-ጾታዊ ጥቃት ቀን ወይም የነጭ ሪባን ቀን አመታዊ የንቅናቄ መርሐግብር መጠናቀቅን አስመልክቶ ነው።

በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ እንደገለፁት በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈጸም ፆታን መሠረት ያደረገ ጥቃት ለመከላከል እና ጥቃት ከደረሰም በኃላ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የአሰራር ማዕቀፎችን፣ የአገልግሎት ስርዓትን በመዘርጋት፣ የግንዛቤ ማስጨበጫዎችን በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። ማንኛውም ዓይነት ወሲባዊ ጥቃት ከሚስከትለው የሰብአዊ መብት ጥሰት ባሻገር በግልም ሆነ በማህበራዊ ህይወት ላይ የሚያሳድረውን ከፍተኛ ተፅዕኖ ለመቀነስ የአንድ ማዕከል አገልግሎቶችን በተጠናከረ መልኩ መደገፍ እንደሚገባ ጠቁመዋል። ዛሬ የተደረገውም ድጋፍ ይህን አጠናክሮ ማስቀጠል የሚያስችል ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

በዛሬው ዕለት ለማዕከሉ የተደረገው ድጋፍ የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች፣ የሴቶች የውስጥ አልባሳት፣ የምግብ ፍጆታዎችና የፅዳት ቁሳቁሶች ይገኙበታል።

Please follow and like us: