የወጣት ማዕከላት የተቋቋሙለትን ዓላማ መወጣት የሚያስችላቸውን ቁመና የማስያዝ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ

የወጣት ማዕከላት የተቋቋሙለትን ዓላማ መወጣት የሚያስችላቸውን ቁመና እንዲይዙ የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሙና አህመድ ገለጹ።
‎‎የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታዋ ክብርት ሙና አህመድ እንዳሉት፤ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የክልል ከተሞች በርካታ የወጣት ማዕከላት ተቋቁመዋል፡፡ ማዕከላቱ ከማዘውተሪያነት ባለፈ ወደ ስብዕና ማበልጸጊያነት እንዲሸጋገሩ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡
‎በዚህ ረገድ ዘመኑን የሚመጥኑ ቴክኖሎጂዎችን አካቶ መጠቀም፣ የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠትና የወጣት ማዕከላትን ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ማድረግ ላይ ውስንነቶች መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡‎ማዕከላቱ የወጣቶችን ስብዕና የማበልጸግ ሚናቸውን መወጣት የሚያስችላቸው ቁመና ላይ እንዲደርሱ የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል፡፡
‎ የክልሎች ባለድርሻ አካላትም የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ ‎በቀጣይ በተለያዩ ከተሞች ያሉ የወጣት ማዕከላትን የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶች በመፍታት ለችግሮቹ ዘላቂ እልባት ለማበጀት ርብርብ እንደሚደረግ ተናግረዋል። ለማዕከላቱ የሚደረገው ድጋፍና ክትትል በተጠናከረ መልኩ ተግባራዊ እንደሚደረግም አስታውቀዋል፡፡

Please follow and like us: