‎ለአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የ 1 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደረገ

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አለም አቀፉ የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ቀን ምክንያት በማድረግ ከ 1 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች ለአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ድጋፍ አደርጓል።

‎የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሙና አህመድ በርክክብ መርሐግብሩ ላይ ጥቃት የሰብዓዊ መብት ጥሰት መሆኑን ገልፀዋል። ‎አመለካከቱንም ድርጊቱንም ለማውገዝና ለመከላከል እየተካሄደ ካለው የግንዛቤና የንቅናቄ ስራ ባሻገር የጥቃት ተጎጂ ሴቶችና ሕፃናት ተገቢው ድጋፍ እና እንክብካቤ እንዲያገኙ ማድረግ ይገባል ብለዋል። ‎ለዚህም ሚኒስቴሩ ከባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመተባበር ሰፊ ስራ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለማዕከሉ የሚውሉ የ 1 ሚሊዮን ብር የሚገመት የህክምና፣ የምግብ፣ የአልባሳትና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።

‎‎የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ስራ አስኪያጅ አቶ ደጀኔ ገመቹ በበኩላቸው፥ ለተደረገላቸው ድጋፍ በማመስገን በሆስፒታሉ እየተሰጠ ያለውን የአንድ ማእከል አገልግሎት አስጎብኝተዋል።

Please follow and like us: