የባሕር በር አስፈላጊነትን አሳንሰው የሚመለከቱ አፍራሽ አስተሳሰቦችን ወጣቱ በዕውቀት ሊመክት ይገባል

የባሕር በር አስፈላጊነትን አሳንሰው የሚመለከቱ አፍራሽ አስተሳሰቦችን ወጣቱ በዕውቀት እና በአንድነት ሊመክት እንደሚገባ ተገለፀ።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን “የባሕር በራችን፣ የደም ሥራችን” በሚል መሪ ሀሳብ ሀገር አቀፍ የወጣቶች ንቅናቄ መርሐ ግብር አካሂዷል። በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሙና አህመድ፥ ወጣቶች ከባሕር በር ጋር የተያያዙ ዕድሎችን በመጠቀም በንግድ፣ በኢኮኖሚ፣ በኢንዱስትሪ፣ በሎጂስቲክስ፣ በሥራ ፈጠራ እንዲሁም በቴክኖሎጂ ዘርፎች ላቅ ያለ ሚና እንዲጫወቱ ይጠበቃል ብለዋል። ወጣቶች የአባቶቻቸውን ተስፋ እና ሕልም ተሸክመው የንግድ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ የሕልውና ጉዳይ የሆነውን የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ለማሳካት ደማቅ ታሪክ የሚጻፍበትን ዕድል መጠቀም ይኖርባቸዋል ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ።

ቅድመ አያቶቻችን ለነፃነት በጀግንነት የከፈሉትን መስዋዕትነት፣ ዛሬም ወጣቱ የሀገርን ጥቅም በዕውቀት እና በጋራ ለማስከበር ተራው ነው ሲሉ አስገንዝበዋል። በውይይቱ ተሳታፊ የነበሩ ወጣቶች በበኩላቸው፥ ለሀገር ጥቅም በጋራ ለመቆም ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

Please follow and like us: