Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋራ
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በአዳስ አበባ ከተማ አስተደዳደር የተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ወገኖች ማዕድ የማጋራት መርሐግብር አካሂዷል።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ክብርት ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ከብርት ሙና አህመድ፣ የሴቶችና ሕፃናት ዘርፍ ክብርት ሒክማ ኸይረዲንን ጨምሮ የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚና ሌሎች የአስተዳደሩ አመራሮች በተስፋ የምገባ ማዕከል በመገኘት ማዕድ አጋርተዋል።ክብርት ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት፤ መንግስት አቅመ ደካሞችንና በዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን ለመደገፍ የሚያስችሉ ሰው ተኮር ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልፀው በዓሉን በጋራ ማክበር በመቻሉም መደሰታቸውን ተናግረዋል።በቀጣይም በመደጋገፍና በመረዳዳት ዜጎች ብሩህ ተስፋ እንዲኖራቸውና የተሻለ ህይወት መምራት እንዲችሉ በቅንጅት እንሰራለን ብለዋል።
በዓሉ የደስታ ፣ የፍቅር፣ የሰላምና የመተሳሰብ እንዲሆን ተመኝተዋል።



Please follow and like us:
