Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
5 ሚሊዮን የበጎ ፈቃደኛ አገልግሎት አሰልጣኞችን በማፍራት፣ 5 ሚሊዮን ህፃናትን የዘላቂ የማህበራዊ ጥበቃ ፕሮግራም አገልግሎቶች ተጠቃሚ ማድረግ!
በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና በአሊያንስ ኬር ናው (Alliance Care Now) መካከል የሦስትዮሽ የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ፡፡

አካታችና ዘላቂ የማህበራዊ ጥበቃን ተግባራዊ ለማድረግ፣ በተለይም የህፃናት መብት ጥበቃና ደህንነት፣ የቤተሰብ እና የሴቶችን የችግር ተጋላጭነት በዘላቂነት ለመፍታት የእምነት ተቋማት አስተምህሮ እና የአማኞች ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን በመጥቀስ የስምምነቱን አስፈላጊነት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) ገልፀዋል ። በሦስትዮሽ ስምምነቱ እርስ በርስ ያለውን ትብብርም በማጠናከር፣ በራስ አቅም ያሉብንን የማህበራዊ ችግሮች በዘላቂነት በመፍታት ተጋላጭ ዜጎች በሀገሪቱ የማህበራዊ ልማትና የደህንነት ማዕቀፎች ውስጥ ተካተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ትልቅ አቅም እንደሚሆን ጠቁመዋል።

በስምምነቱ ከተካተቱ የትብብር መስኮች መካከል የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን በቅንጅት በመምራት 5 ሚሊዮን የበጎ ፈቃደኛ አሰልጣኞችን በማፍራት፣ የሀገር ውስጥ ጉዲፈቻና ሞግዚትነት እንዲሁም የአደራ ቤተሰብ እንክብካቤን ማበረታታት ብሎም ጾታዊ ጥቃትን፣ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን እና የሱስ ተጠቂነትን መግታት የሳተላይት ክሊኒክ አገልግሎት መስጠት የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
Please follow and like us:
