Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ለ50 ሺህ ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችል የ2.3 ሚሊዮን ዩሮ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና አምረፍ ሄልዜ አፍሪካ በወጣቶች ዲጂታል አካታችነት እና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ እና ለ50 ሺህ ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችል የ2.3 ሚሊዮን ዩሮ የፕሮጀክት ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የአምረፍ ሄልዝ አፍሪካ ሀገራዊ ፕሮግራም ዳይሬክተር ምስራቅ መኮንን ተፈራርመዋል። ፕሮጀክቱ አዲስ አበባን ጨምሮ በአምስት ክልሎች እንደሚተገበር በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል።
በቀጣይም ፕሮጀክቱን የበለጠ ለማስፋትና ዘላቂነት ባለው መልኩ ለማስቀጠል ተቋማቱ በጋራ ለመስራት ተሰማምተዋል።
Please follow and like us:
