Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወር አበባ ጤናና ንፅህና አያያዝን ተደራሽ ለማድረግ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችን ሁለንተናዊ መብት ለማስከበር፣ ተሳትፏቸውን ለማሳደግና ተጠቃሚነታቸውንለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየ ሲሆን፣ የወር አበባ ጤናና ንፅህና አያያዝን (MHH) ማሻሻል ከነእዚህጥረቶች መካከል አንዱና ዋነኛው ነው።እንደሚታወቀው፤ የወር አበባ ተፈጥሯዊ እንጂ ምርጫ አይደለም። የወር አበባ ትውልድን ለማስቀጠል ለሴቶች የተሰጠየተፈጥሮ ጸጋ ነው። ለዚህም ሚኒስቴሩ የወር አበባ ጤናና አያያዝን እንዲሁም የንፅህና መጠበቂያ ፓድን ተመጣጣኝ እናተደራሽ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል። ሆኖም በየጊዜው ከሚከሰቱ አለም አቀፋዊ ሁኔታዎች በተጨማሪ ከምርት አቅርቦት፣ ከውጭ ምንዛሪ እጥረት፣ ከኑሮ ውድነትናከተደራሽነት ጋር በተያያዘ ክፍተት እንዳለና ይህም በተጠቃሚዎች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ይታመናል። ቀደምሲልመንግስት የችግሩን አሳሳቢነት በመገንዘብ ከውጭ በሚገቡ የንፅህና መጠበቂያ ፓድ ምርቶች ላይ ከፍተኛ የቀረጥ ቅናሽማድረጉና በተለይ ከ2014 ዓ.ም በፊት ከነበረበት ከ30 በመቶ ወደ 10 በመቶ በማውረድ በዝቅተኛ ዋጋ እንዲጠቀሙየሚያስችል አበረታች እርምጃ መውሰዱ ይታወሳል።
የወር አበባ ንፅህና አጠባበቅ ተግዳሮትን በዘላቂነት ለመፍታት የሚደረገው ጥረት ከተቋም የተሻገረ ትብብርን የሚጠይቅበመሆኑም ከጤና ሚኒስቴር፣ ከትምህርት ሚኒስቴርና ሌሎች የመንግስት ተቋማት ጋር በጋራ እየተሰራ የሚገኝ ሲሆንበቅርቡም አለም አቀፍ ሁኔታውን ተከትሎ የተከሰተውን የዋጋ ጭማሪ አስመልክቶም ሚኒስቴሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋርውይይት እያካሄደ ይገኛል። እነዚህ ጥረቶች በተለይም ተማሪዎች በወር አበባ ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩናበትምህርታቸው ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ።
ከተግባራዊ ስራዎች አንጻር ፦
ከቱርክዬ የልማት ድርጅት(TICKA) ጋር በመተባበር መልሶ ጥቅም ላይ የሚውሉ (Reusable) ፓዶችን በማምረት
አቅም ለሌላቸው የዩኒቨርሲቲና የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንዲቀርቡ እየተደረገ ሲሆን፣ ጥቅም ላይ ከዋሉ በኋላ የሚጣሉ (Disposable) ፓዶችንም የማሰባሰብና የማሰራጨት ስራም በስፋት እየተከናወነ ነው።
በተጨማሪም በትምህርት ቤቶች የፓድ ማከፋፈያ ማሽኖችን (Dispensing Machines) የመትከል ተሞክሮ የተጀመረ ሲሆን፣ ይህንን አገልግሎት ይበልጥ ለማስፋፋት ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል።የንዕህና መጠበቂያ ፓድ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ ለማድረግ የሚከናወኑ ተግባራትን በበላይነት የሚመራ፣ ግንዛቤን የሚያሰርፅ፣ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን የሚቀርጽና ፍትሃዊ ስርጭትን የሚያረጋግጥ ብሔራዊ መሪ ኮሚቴ (National Steering Committee) ተቋቁሞ ወደ ስራ የተገባ ሲሆን፣ ይህ ኮሚቴ በስሩ ከ70 በላይ የመንግሥት፣ የግል ሴክተር እና የልማት አጋሮችን ያቀፈ የምክክር መድረክን (MAP-PPD) ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ ነው።
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (EiTEX) 98% ጥሬ እቃቸው በአገር ውስጥ ከሚገኙት ከእንሰትና ከቀርከሃ የሚመረት ባዮሎጂካል ፓዶችን የመፍጠር ስኬት ያስመዘገበ ሲሆን፣ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣንም (EFDA) እነዚህን ምርቶች “ዝቅተኛ አደጋ የሕክምና መሣሪያ” በሚል ምድብ ውስጥ በማካተት የጥራት ስጋቶችን ለመቅረፍ ምላሽ ሰጥቷል።
በቀጣይም አምራቾችን ከማሽነሪ ግዥ አጋሮች ጋር በማገናኘት እና የገበያውን መረጋጋት በማረጋገጥ ረገድ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እንዲሁም ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በትኩረት የሚሰራ ሲሆን፣ የሀገር ውስጥ አምራቾችን ለማበረታታትም ልዩ ልዩ ጥናቶች እየተደረጉ ይገኛል። ይሁን እንጂ የሴቶች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ አቅርቦትን ለማሳደግ፣ አቅምን ባገናዘበ እና ንፅህናውን በጠበቀ መልኩ ለሁሉም በሁሉም ቦታ ተደራሽ ለማድረግ አሁንም ሰፊና ቀጣይነት ያለው ስራ በቅንጅት መስራት የሚገባ በመሆኑ የሚኒስቴር መስሪያቤታችን ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር የተጀመረውን ሰራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል እየገለጸ ለስኬታማነቱም የድርሻቸውን እንዲወጡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጥሪው ያቀርባል።
