በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የተከናወኑ የልማት ሥራዎች ተገመገሙ

በሴቶችና ማህበራዊጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የተመራ የፌደራል ሱፐርቪዥን ቡድን፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በካፋና ቤንች ሸኮ ዞኖች ያደረገውን የመስክ ምልከታ ተከትሎ ግብረመልስ ሰጠ።

‎‎የሱፐርቪዥን ቡድኑ የ”መሶብ” የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ የኮሪደር ልማት፣ የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ፣ የደንቢ ኢኮ ሎጅ እና የሌማት ትሩፋት ሥራዎች አበረታች መሆናቸው ተገልጿል። በተጨማሪም በክልሉ ያለውን እምቅ ሀብት በመጠቀም የሥራ ዕድል ፈጠራን ማሳደግ፣ የገበያ መረጋጋትን ማረጋገጥ እና የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን በጥራትና በፍጥነት ማጠናቀቅ እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጧል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የተገኙ ውጤቶችን በማጠናከርና የታዩ ክፍተቶችን በማረም የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መንግሥታቸው በቁርጠኝነት እንደሚሠራ መግለፃቸውን ከክልሉ ኮሚዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

‎የክልሉ መንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን በበኩላቸው፣ ለ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ትኩረት መሰጠቱን ጠቁመዋል ሲል የደቡብ ምዕራብ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።

Please follow and like us: