‎የ ‘Human Capital Operation’ የ2018 አፈፃፀም እና የ2019 እቅድ ዝግጅት ላይ ወይይት ተካሄደ

‎(ግንቦት 30/2018 ዓ.ም) የ2018 በጀች አመት የ’Human Capital Operation’ ትግበራ እና የቀጣይ አመት እቅድ ዝግጅት ዙሪያ ከክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስተባባሪዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል::

‎በመድረኩ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ አቶ ቦጋለ ጣሰው፥ ፕሮጀክቱ በዋነኝነት በስርዓተ ምግብ፣ የአሰራር ስርዓትን በማጠናከር እንዲሁም እውቀትና ክህሎት በማሻሻል የቀጣይ ትውልድ ምርታማነትን ለማጎልበት አላማ አድርጎ የሚተገበር መሆኑን አብራርተዋል። በፕሮጀክቱ ታዳጊ ሴቶች፣ ህፃናት፣ አካል ጉዳተኞች እና ለችግር የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን በተለያዩ የማህበራዊ አገልግሎቶች ተካታችነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያግዙ ስራዎች መከናወናቸውን ስራ አስፈፃሚው ገልፀዋል።

‎‎ፕሮጀክቱ ከአለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በአገሪቱ በተመረጡ 65 ወረዳዎች ላይ እየተተገበረ እንደሚገኝ አስታውሰዋል። ለተግባራዊነቱም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅትና በትብብር ሲሰሩ መቆየታቸውንና ጅምር ውጤቶች በየዘርፉ መመዝገባቸውን ጠቁመዋል።‎ፕሮጀክቱን ወደ ስራ ለማስገባት ግንዛቤ ከማስጨበጥ ጎን ለጎን ፍላጎትን የመለየትና መረጃ የመሰብሰብ ስራ በትኩረት መሠራቱን ተመላክቷል

 

Please follow and like us: