ወሰን ተሻጋሪ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ ለሚሳተፉ ወጣቶች ኦረንቴሽን ተሰጠ

“በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል ለአምስተኛ ጊዜ የሚከናወነው የ2018 ዓ.ም ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ ለሚሳተፉ ወጣቶች ኦረንቴሽን ተሰጥቷል።
‎‎የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሙና አህመድ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለህይወት ስንቅ የሚሆን መልካም ተግባር የሚከወንበት መሆኑን ጠቁመዋል። ‎አገልግሎቱ በመንግስትና በሕዝብ መካከል ጠንካራ ትስስር እንዲፈጠር ከማድረግ ባሻገር የመረዳዳት እሴቶች በሕዝቡ ዘንድ እንዲጎለብቱ እያስቻለ መሆኑን  ገልፀዋል። በዘንድሮው ወሰን ተሻጋሪ የበጎፈቃድ አገልግሎት የአረንጓዴ አሻራ፣ የትውልድ ግንባታ፣ የቤት ግንባታ፣ የደም ልገሳ እና የሰላም ግንባታ ላይ በትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
‎

እንዲሁም በሌሎች የስራ ስምሪቶች እንደየአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ ጥራት ባለውና ትውልድን ሊያስተምር በሚችል መልኩ መስራት ይጠበቅባችዋል በማለት አስገንዝበዋል። ‎በጎ ፈቃደኞች በራሳችሁ ተነሳሽነት በቅንነት በምትሰጡት አገልግሎት ህዝባችሁን፣ ክልላችሁን እና ሀገራችሁን እንደምታኮሩ ተስፋ አደርጋለው በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

Please follow and like us: