Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ሀገር አቀፍ ወሰን ተሻጋሪ የክረምት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጀመረ
“በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ ፭” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው የዘንድሮ ወሰን ተሻጋሪ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በዛሬው ዕለት በሀዋሳ ከተማ በይፋ ተጀመሯል።
የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በዚሁ ጊዜ፥ “በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከንፁህ ህሊና የሚመነጭ መልካም ተግባር ነው። ማገልገል ክብርና መታደል ነው።” በበጎነት ሀገርንና ወገንን ማገልገል ደግሞ የሰውነት ውሃ ልክ መሆኑን ተገንዝበው በቅንነትና በራስ ተነሳሽነት እያገለገሉ ያሉ ወጣቶችን አመስግነዋል። በዘንድሮ የክረምት ወራት 25 ሚሊዮን በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን በ14 የስምሪት መስኮች እንዲሰማሩ በማድረግ 53 ሚሊዮች በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን ገልፀዋል።
ከ61 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የህዝብና የመንግስት ወጪ በማዳን በመንግስትና በማህበረሰቡ ያልተሸፈኑ የልማት ሥራዎችና ማህበራዊ አገልግሎቶች እንደሚከናወኑ ጠቁመዋል። በተለይም “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄን መርሐግብር እንዲሳካ ሁሉም ወጣት እና ህዝባችን ሁሉንም አቅሞች በመጠቀም በንቃት በመሳተፍ ደማቅ የዜግነት አሻራቸውን እንዲያሳርፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
Please follow and like us:
