“በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የግል ምቾታችሁን ትታችሁ በየአካባቢው ያሉ አቻዎቻችሁን፣ የነገ ተተኪ ታዳጊ ህፃናትንና መላውን ህብረተሰብ ለበጎ ስራ በማነቃቃትና በተግባርም ጭምር በመሳተፍ ላበረከታችሁት አስተዋፅዖ ከልብ እናመሠግናለን” ‎- ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ

በተለያዩ ክልሎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሲሰጡ ለነበሩት የወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የምስጋና መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡

‎በተዘጋጀው የምስጋና መርሃ ግብረ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ÷ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት መተጋገዝንና መተሳሰብን ከማጎልበትና የሀገራችን ገፅታ በመልካም ከመለወጥ ባለፈ ወጣቶች የአካባቢን ባህል እና ወግ ለመለዋወጥ እገዛ አድርጓል ብለዋል። ‎ተግባሩ በመንግስት ያልተሸፈኑ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ክፍተቶች ለመሙላትና የማህበረሰብ ችግሮችን ለመፍታትም ጉልህ አስተዋፅዖ እያበረከተ መሆኑን ጠቅሰዋል።
‎‎የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እንደሀገር አርያነት እና ተምሳሌት ሆነው በተግባር ጭምር ለበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለሰጡት ትኩረትና ላሳዩት የላቀ አመራር ከፍተኛ አክብሮት እና ምስጋና አቅርበዋል።

‎በመርሐግቡሩ የተሳተፉ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የግል ምቾታቸውን በመተው በቆይታቸው አቻዎቻቸውን፣ የነገ ተተኪ ታዳጊ ህፃናትንና መላውን ህብረተሰብ ለበጎ ስራ በማነቃቃት በተግባር በመሳተፍ ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅዖ አመስግነዋል። ‎ፕሮግራሙ የተሳካ እንዲሆን በየደረጃው የላቀ አስተዋፅዖ ላባረከቱ በጎ ፈቃደኞች፣ የፀጥታ አካላት፣ የክልል አመራሮችና የሚዲያ ተቋማት ምስጋና አቅርበዋል።

‎‎የዘንድሮው መርሐግብር ሀገራችን ኢትዮጵያ ከሁሉም ማዕዘናት ከሁሉም የህብረሰብ ክፍሎች የተወከሉ ዜጎች ችግሮቻችን ለመፍታት በጋራ እየመከሩ በሚገኙበት ታሪካዊ ወቅት መካሄዱ ልዩ ያደርገዋል፤ ይህንኑ የአንድነትና የትብብር መንፈስ የበለጠ የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል። ‎እንደሀገር የተጀመሩ የበጎ ፈቃድ ስራዎች ከክረምት ባሻገር በበጋውም ተጠናክረው እንዲቀጥሉና ሁሉም በንቃት እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል።
‎

Please follow and like us: