በተቀናጀ አሰራር የተጋላጭ ወገኖችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የ“GO-NGO” ፎረም በድጋሚ ለማቋቋም የሚያስችል ምክክር ተካሄደ

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መንግስታዊ እና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት መካከል የትብብርና ቅንጅት ሥራዎችን ለማጠናከር፣ የ“GO-NGO” ፎረም ዳግም ምሥረታ መድረክ በአዲስ አበባ አካሂዷል።

‎በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክብርት ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሳልፈው አመዲን እንደገለጹት፤ ሴቶች፣ ሕፃናት፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያን እና ሌሎች ተጋላጭ የማኅበረሰብ ክፍሎችን በባለቤትነትና በተቀናጀ መልኩ ለመደገፍ አሁን ላይ ጠንካራ የትብብር ማዕቀፍ መዘርጋት ወሳኝ ነው። ‎ቀደም ሲል ተቋቁሞ የነበረው ይህ ፎረም ከተቋማዊ መዋቅር ለውጥ ጋር ተያይዞ ተቋርጦ መቆየቱ ሥራዎች በተበጣጠሰ መልኩ እንዲከናወኑና የተሻለ የሀብት አጠቃቀም እንዲኖር ማድረጉ ተነስቷል።

‎አሁን ዳግም የተቋቋመው ፎረም ይህንን ክፍተት በመዝጋት የሥራ ድግግሞሽን በማስቀረት፣ ተጠያቂነትን በማጠናከር እና ሀብትን በአግባቡ በማስተባበር ተጨባጭ ውጤት እንደሚያስመዘገብ ታምኖበታል። ‎ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከተሰጠው ኃላፊነት አንጻር ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ላደረገው ትብብር ምስጋና ያቀረበ ሲሆን፤ በቀጣይም ለፎረሙ ስኬታማነት የቴክኒክና የፋይናንስ ድጋፍ ላደረገው ዪኤንውመን(UN WOMEN) እና ለተባበሩ አካላት ሁሉ ልባዊ ምስጋና አቅርቧል።
‎
‎

Please follow and like us: