ሚኒስቴሩ የኀብር ቀንን አስመልክቶ ለተቋሙ ሰራተኞች የበዓል መዋያ ስጦታ እና ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ማዕድ አጋራ

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሮችና ባለሙያዎች “ብዝኀነት የኢትዮጵያ ጌጥ!” በሚል መሪ ሃሳብ የኀብር ቀንን በተለያዩ መርሐግብሮች በድምቀት እያከበሩ ይገኛል።

‎ሚኒስቴሩ የህብር ቀንን እንዲሁም መጪውን አዲስ አመት ምክንያት በማድረግ የተቋሙ ሰራተኞች ከነቤተሰባቸው በዓሉን ተደስተው እንዲያሳልፉ አስፈላጊውን የበዓል መዋያ ድጋፍ አድርጓል። በተጨማሪም አቃቂ ቃሊቲ ለሚገኘውና ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ማረፊያና የልማት ማህበር የ200 ሺህ ብር እና የቴምር ድጋፍ ተደርጓል። በተመሳሳይ ለ13 የበጎ አድራጎት ተቋማት የቴምር ድጋፍ አበርክቷል።
‎‎በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የክብርት ሚኒስትር አማካሪ ክቡር አቶ ጌታቸው በዳኔ በዕለቱ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ብዝሃነት ለሀገር ጥንካሬ እና ለህዝቦች ማህበራዊ ትስስር የጸና ምሰሶ መሆኑን አንስተዋል። ‎የኅብረ ብሔራዊ አንድነት እሴቶችን ማጠናከር ሀገርን ከማፅናት ባለፈ የነገዋን የበለጸገች ሀገር ዕጣ ፈንታ የሚወስን ቁልፍ ጉዳይ እንደሆነም ገልጸዋል።
‎
‎ዛሬ ከምንጊዜውም በላይ በህብረት የመቆሙን አስፈላጊነት ተረድተን ለጋራ ቤታችን በጋራ መትጋት ይገባናል ሲሉም አሳስበዋል። ‎በልዩነታችን አምሮብን፣ በአንድነታችን ጸንተን፣ ለጋራ ብልጽግናችን በህብር መቆምና በየተሰማራንበት መስክ ጠንክረን መስራት ከሁላችንም ይጠበቅብናል ብለዋል።
‎
‎

Please follow and like us: