በየዘርፉ የተመዘገቡትን ተጨባጭ ውጤቶች ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እና እንደሀገር የተጣለብንን ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ቁርጠኛነትና በላቀ ትጋት መረባረብ ይጠበቅብናል – የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ርክክብ እና ተቋማዊ ትውውቅ አዲስ ለተሾሙት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ እና ለክቡር አክሊሉ ታደሰ (ዶ/ር) የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር የስራ ርክክብ አደረጉ።
በርክክቡ ወቅት አጠቃላይ የተቁዋሙ የቁልፍ ተግባራት የ5 ዓመት አፈጻጸም (የ2014-2018) የፕሮጀክቶችና የመግባቢያ ስምምነቶች እንዲሁም የአስተዳደር የስራ ክፍሎች ስራዎች የ 5 ዓመታት የተግባራት አፈጻጸምና በቀጣይ የአዲሶቹን አመራሮች ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች በዝርዝር ቀርበዋል፡፡ በስራ ርክክቡ ወቅት የቀድሞ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) አዲሶቹ የተቋም አመራሮች በየዘርፉ ለባለፉት አምስት ዓመታት እያደገ የመጣውን ውጤታማነት አጠናክሮ በማስቀጠል ህብረተሰቡን በላቀ ደረጃ ተጠቃሚ ለማድረግና ሴክተሩን ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማድረስ በበለጠ ቁርጠኛነትና በላቀ ትጋት እርስ በእርስ በመደጋገፍና በመደመር እሳቤ እንዲያስቀጥሉ አደራ ብለዋል፡፡

በተለይም ከልማት አጋሮችና ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሀብት በማሰባሰብና ሰፋፊ የሆኑና ተተግብረው ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረጉ ፕሮጀክቶችን እና በመተግበር ሂደት ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን አፈጻጸም ውጤታማነትን፣ በሀብት አጠቃቀም እና አጠቃላይ ስራዎችን በመምራት ረገድ የታዩ የሴክተሩን ውጤቶችን አዲሶቹ አመራሮች በተሻለ ሁኔታ እንደሚያስቀጥለቸው እምነቴ ጽኑዕ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ እስካሁን የተጀመሩትን ስኬታማ ስራዎች አጠናክረን አዳዲስ ስኬቶችን ለማስመዝገብ እና በሴክተሩ አሻራችንን ለማስቀመጥ በተሰጠን ጊዜና ሰፊ ዕድል በፍጹም ቁርጠኝነትና ትጋት እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ለዚህም በተቋሙ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና ሠራተኞችን ጨምሮ ባለድርሻና አጋር አካላት በቅንጅት እና በጊዜ የለኝም መንፈስ ለላቀ ውጤትና ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት እንዲሠሩም ክብርት ሚኒስትሯ ጥሪ አቅርበዋል። የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር አክሊሉ ታደሰ (ዶ/ር) በበኩላቸው የወጣቶችን የልማት ተካታችነት እና ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በከፍተኛ ተነሳሽነት ለወጣቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እና ለስፖርቱ ዘርፍ ዕድገት እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡
Please follow and like us: