በዜጎች ህይወት ላይ የሚጨበጥ ለውጥ ለማምጣትና የብልፅግና ጉዞውን ለማሳካት በቁርጠኝነት እንሰራለን!

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ እና የመጀመሪያው ሩብ ዓመት አፈፃፀም ውይይት ተጠናቅቋል።
ባለፉት ዓመታት በሴክተሩ የተከናወኑ በርካታ ስራዎች አበረታች ውጤት ያስመዘገቡ መሆናቸው በመድረኩ ተነስቷል። ተቋምም ሆነ ሀገር የሚገነባው በቅብብሎሽ በመሆኑ፤ ቀጣይ ተልዕኮዎችን በታላቁ የመደመር እሳቤ በመቃኘት፣ የተሟላ እይታ በመያዝ እና እሴት በመጨመር የተጀመሩ ስራዎችን የበለጠ ለማላቅ በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ እንሚያስፈልግ ተገልጿል።
የዜጎችን የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶች ውጤታማ የሚሆኑት በየደረጃው የሚገኙ አመራርና ፈጻሚ አካላት የተቀናጀና የተናበበ አካሄድ ሲከተሉ እንደሆነ ተመላክቷል።
ከአፈፃፀም ሂደት አንፃር ከፖሊሲ፣ ከመዋቅር፣ ከሪፎርም፣ ከመልካም አስተዳደር እና ከቁጥጥር አኳያ የታዩ ውስንነቶችን በመለየት በዘላቂነት ለመፍታት በላቀ ትጋት ይሰራል ተብሏል።
በበጀት ዓመቱ የታቀዱ ቁልፍ ተግባራት በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብና በጥብቅ ሙያዊ ዲሲፕሊን መፈጸም እንዳለባቸው አቅጣጫ ተቀምጧል። ግልፅነትን ለመፍጠር፣ የተልእኮዎችን ግንዛቤ ለማሳደግ እና የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ የሚያስችሉ የምክክር መድረኮች በነደረጃው ተጠናክረው እንደሚቀጥለለ ተጠቁሟል።
አመራሩ የሴክተሩን የተሻጋሪነት ባህሪ ማዕከል በማድረግ እና ያለውን ሰፊ አቅም በማቀናጀት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር መንፈስ ለመስራት ዝግጁና ቁርጠኛ መሆኑንም አረጋግጧል።
Please follow and like us: