Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
7ኛው አጠቃላይ ሀገራዊ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ፣ የኢፌዴሪ ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መላው የሀገራችን ሴቶች፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያንና አደረጃጀቶች ላበረከቱት አስተዋፅኦ ምስጋና ያቀርባል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች በተመዘገቡበት በዚህ ታሪካዊ ምርጫ፣ ድምፅ በመስጠት ብቻ ሳይወሰኑ እንደ ምርጫ አስፈጻሚ፣ ታዛቢና ዕጩ ተወዳዳሪ በመሆን ግንባር ቀደም ሚና ለተጫወቱት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሴቶች፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን እንዲሁም አደረጃጀቶቻቸው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በታላቅ አክብሮት ያመሰግናል።
ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ ያሳያችሁት ሰላማዊነት፣ ስነ-ምግባር፣ ንቁ የዜግነት ተሳትፎ እና ከፍተኛ የድምፅ አሰጣጥ ቁጥር እናንተ የሀገሪቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ብቻ ሳትሆኑ የዛሬው የለውጥ ምህዋር ዋነኛ ስትራቴጂክ ኃይል መሆናችሁን ያስመሰከራችሁበት ታሪካዊ ሂደት ነውና እናመሠግናለን። የዴሞክራሲንና የሰላምን መንገድ በመምረጣችሁ እና ለሚቀጥለው ትውልድ አርአያ የሚሆን ተግባር በመፈጸማችሁ ሚኒስቴሩ ከፍ ያለ ምስጋናውን ያቀርባል።
አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞችና ልዩ ድጋፍ የሚሹ ወገኖች ያሉባቸውን የተለያዩ ፈተናዎች ተቋቁማችሁ በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ብሔራዊ መብታችሁን ለመጠቀምና የዜግነት ግዴታችሁን ለመወጣት ላሳያችሁት ተነሳሽነት እንዲሁም በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችና ሴቶች በምርጫው ሂደት ሁሉ ሰላማዊና ደጋፊ የሆነ አካባቢን በመፍጠር ላበረከታችሁት የላቀ አስተዋጽኦ ሚኒስቴሩ አክብሮቱን ይገልፃል።
ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
